Girma Bireye

A Son’s Trubute

 

ግርማ ስለ ልጆቹ አውርቶ አይጠግብም” ስንቶቻችሁ ብላቹ ታቃላቹ?”

ስንቶቻችሁስ “ግርማ እኮ እንደሱ ልጆች ልጅ ያለ አይመስለውምአንዳንዴማ የሚጨማምርበት ነው የሚመስለው:” ብላችሁ ያማቹም አትጠፉም።

አዎ አባታችን ስለ ልጆቹ አውርቶ አይጠግብም ነበረ። ደግሞም ትንሿን እንኳን ስኬታችንን አጣጥሞ አና አጣፍጦ ማውራት ይችልበታል።  ይህ high school ተማሪ እያለሁ አንዳንዴ በጣም ያበሳጨኝ ነበር። ምክንያቱም እንደ ትላንት ማታ ለሩጫ የሚያስፈልገኝን ትጥቅ ወይም የምሳ ገንዘብ መስጠቱ ለማይቀር ነገር በሩጫ ጊዜህን ለምን ታጠፋለህ በሚል ስንከራከር አምሽተን፣ በማግስቱ ለBibile Study ተሰብሳቢዎች “ያሬድ እኮ ባለፈው የሩጫ ውድድር ነበረው 2ተኛ ወጥቶ ሜዳልያ ተሸለመ እና ነገም ሌላ ውድድር አለው” ብሎ ሲያወራ እሰማዋለሁ። For the record ሁለተኛ ወጥቼ ባውቅም I was not that good! But that’s my father. He loves talking about his children and their little and no so little accomplishments.

I realized this more just a few weeks ago, አንድ ወዳጄ Finland ድረስ ደውሎ አባቴን በሚሰራበት ሆስፒታል ባጋጣሚ እንዳገኘው እና አባቴ በጣም ጠንካራና ተስፋ የሞላበት ሰው እንደሆና ካወጋኝ በኋላ፣ “እዛ ለነርሶቹ ሁሉ የሚያወሩት 4 ልጆች እና 5 የልጅ ልጆች እንዳደረሱ ነበር ” አለኝና ብዙ አወራኝ። This is when I again realized የአባቴ ትልቁ የህይወት ሥኬቱ እና ኩራቱ እኛ ልጆቹ እንደሆንን የተረዳሁት::

ግን ግርማዬ often times የልቡን እያወራንም ነበር። በጥናት የተደገፈ መሆኑን እርግጠኛ ባልሆንም ብዙዎች ይህ የሃበሻ አባቶች ችግር ነው ይላሉ። ለሁሉም ሃበሻ አባቶች ስለማይሆን በኢትዮጵያ ዳያስፖራውዎች common ነው ብለን እንለፈው። ማለቴ እንደኛ አባት ኢትዮጵያ ተወልደው እና ጎልምሰው አሜሪካ የመጡ ማለት ነው።

ወደ ቁምነገሬ ልመለስ፣

A few years after Girmaye first got sick and recovered, he visited me in Ethiopia for a few months and we once set out on a road trip to the beautiful bale mountains. አዲስ አበባ የገዛኋት አንድ ቀይ ቪትስ ነበራችኝ። እሷን ይዘን ያን ከአስርት አመታት በፊት ጭቃና ኮሮኮንች ሆኖ የሚያስታውሰውን የባሌ መንገድ በአሰላ ፣ በበቆጂ፣ አዳባ ፣ ዶዶላ ፣ዲንሾና ሮቤ አድርገን ጎባ ያደገበትን ቦታዎችና ዘመዳ ዘመዶች ጠየቅን። ስንመለስ ደግሞ በሻሸመኔ ሃዋሳ አድርገን በህይወቴ ደስ የሚለኝን ጊዜ አሳለፍኩ። And It was one of the most memorable time spent with my Father። I had always wanted a bonding moment with my father to talk and know about his childrenhood life and also his life aspirations and dreams. የውስጥ ሚስጥር “I was also on a mission to convince him to sell the family house።” Needless to say, that did not work so well. Those who knew my father well, know exactly what I am talking about.

I could tell he was incredibly proud; his firstborn Son taking him back down memory lane of his journey getting his family out of a small town called Agarfa in West Arsi Zone, about 30km from the town of Goba – Our long journey to America began on this same road. It is on this road the young Girma packed all of his life belongings and headed 400km North to Addis Ababa to settle his 3 children and young wife in another small town 30km North of Addis called Chancho. Although only 11 years old, I vividly remember this tiring 13hrs journey to Addis, where I got to see a television for the first time in my life. Little did I know then that this was just a little stop to a long journey to Seattle but a 6 long year transition camp for my mother and three siblings in Chancho while they wait to join us in America.

Going back to the recent trip, unlike the first, ግርማዬ ብዙ የህወት ጉዞውን አወጋኝ። ከዚህም ብዙ ነገሮችን ተማርኩኝ። ያው ዕሱ አንዳንድ ከክርስትና ህይወት በፊት የነበሩ ክስተቶችን ሊደብቅና አደባብሶ ሊያልፍ ቢሞክርም, I knew from his close friends they had a lot “fun” than Girmaye like to reveal. I am now in my late twenties, around the same age that he was when we made that previous journey together to Addis Ababa in the mid 90s.

ስለአባታችን የልጅነት እና የጉልምስና ዘመን ሲወራ እንዴት ታታሬ፣ ደፋር፣ ቁምነገርኛ ፣ ያሰበውን እና የፈለገውን ከማሳካት ሁልጊዜ ወደ ኋላ የማይል ሰው እንደሆነ ሳይነሳ አይታለፍም:: ወጣት አስካለም ለስራ ተመድባ ወደ ጋሰራ ስትሄድ እንደዚህ አይነት ጓደኛ ነበር ያጋጠማት ። ታዲያ አይኑ ካርፈባት እናም ሚስቱ ካደረጋት ጀምሮ፣ እሷና የቅርብ ጓደኞቻቸው ሲመሰክሩ፣ ያ የ20 አመቱ ወጣት ግርማ ለናታችን ባል ብቻ ሳይሆን ጓደኛ፣ ወንድም፣ መከታዋና እና የመጀመሪያ ፍቅሯ ነበር።

He was also an an amazing young father.  በኛ በልጆቹ ብቻ ሳይሆን በሰፈር ልጆች በሙሉ እንዴት የተከበረ እና የተፈራ እንደነበረ እኔ እንኳን አስታውሳለሁ። እሱን የምታሸንፈው እህታችን ማህሌት ብቻ ነበረች። አንዳንዴ ከስራ ለምሳ ሲመጣ ከጊቢ ወጥተን በጭቃ የጎርፍ ዝናብ ስንገድብ ይደርስብናል። ታዲያ እሱ ገና ከሩቅ ሲመጣ የሰፈሩ ልጆች ሁሉ ብትን ብለው ወደ እየ ጊቢው ክትት ነበር የሚሉት። እኔና ወንድሜ እዩኤል ግን እጃችንን ተጣጥበን የተለመደችውን አለንጋችንን ለመቅመስ በረንዳ ላይ ነበር የምንጠብቀው። አጅሬዋ ግን ሁል ጊዜ ከነጭቃዋ አልጋ ስር ገብታ ነበር  የምትደበቀው። አስካሁን ትዝ የሚለኝ እንድ ቀን እሷን ከአልጋ ስር አውጥቶ ጓሮ ለጓሮ አልያዝ ብላው ሲያሳድድ ቆይቶ ምሳውንም ሳይበላ ወደ ስራ የተመለሰበትን ነበር።

The first 10 years of the young Girma and Askale were full of adventure and also perseverance. Married when they were both in their early twenties, it was clear from my fathers stories and later testimonies of my mother and their friends that they were undoubtedly in love and were happy and incredibly excited about building their family. It is during this first 10 years that they had four children that today have 5 beautiful children of their own – making them proud grandparents!

And it is this that my father told me is his life’s greatest accomplishment and one that he loves to talk about every opportunity he gets. I mean literary. Just the other day, I found another testimony of this very fact when I walked over to our neighters of 20+ years to tell them about his passing. In the 10+ years I lived in my parent’s house in my young years, I probably talked to this old couple maybe once or at most trice and that is probably about 10 or so years ago. But when I told them I am his oldest son, the lady was quick to say “Are you Yared? When did you come back from Finland.“  I immediately broke down in tears.

It also reminded me of the times in Addis where all of the sudden everyone on the first floor of the Lideta condominium I lived in knew who I was and the fact that I was a “Diaspora from America” and that I was working for an International NGO. Given it was just after his visit, Girmaye was definitely a suspect.

Another thing I learned about my father during the memorable road trip in Ethiopia is that he truly lived his life for us his chilren. If you characterize the first 10 years of his twenties as the times when he met a tall beautiful young lady from Addis Ababa that gave him 4 children, the next 10 years were where he built a rock solid foundation that defined who and where we are all today.

This incredible life journey all started on that same Goba to Addis Ababa road and it eventually led here to Seattle – where he spent the next decade working 16 hours shift with incredible level of commitment, discipline and determination to make something of the new opportunity that is afforded to him to make a better life for his small, (maybe not small) family.  Would you say, ተሳክቶለታል  ?

ከዛ በኋላ ባሉት 10 አመታት እግዚያብሄር በራሱ መንገድ እረፍት አድርና አምላክህን አግልግል ያለበት ጊዜ ነበር እና እሱም በጸጋ ተቀብሎ ትኩረቱን ወደ አምላኩ ያደረገበት እና በልጆቹ የዘራውን  የ hard work እና discipline ፍሬ ያየበት ነበር ማለት ይቻላል።

አባቴ አንድ የህይወት ጸሎት እና ምኞት perhaps ፍርሃት ነበረው። ይህም በእድሜው መጨረሻ ለልጆቹ ሸክም እንዳይሆን ነው። ምክንያቱም በሰው ላይ መወደቅ ካለመፈለጉ በተጨማሪ ለረጅም አመት በNursing Home ከመስራት የመነጨ ነው የሚል ግምት አለኝ። እግዚአብሄርን ለወዳጆቹም ሆነ ለሌሎች ሸክም ሳይሆን ቶሎ ወደማረፊያው እንዲወስደው ይመኝ ነበር እናም በርትቶም ይጸልይ ነበር። እንደውም “ያሬድ ለእኔ አንዳች አታስብ ስለኔ እግዚአብሄር ብቻ ነው የሚያውቀው። አንተ ብቻ የራስህን ህይወት ኑር”  አይነት ንግግር ተናግሮኝ መበሳጨቴ ትዝ ይለኛል።  አሁን ካረፈ በኋላ እናቴ ስታዋጋኝ፣ “አስኪ፣ እኔ በልጅቼም እጅ ቢሆን መውደቅ እንደማልፈልግ ታውቂያለሽ አይደል? አንቺ አካሌ ነሽ ፣አንቺው እንደሚሆን ታደርጊኛለሽ።” ይል ነበር።

አባቴን እግዚአብሄር ወደሱ ሲጠራው ይህን ጸሎት እና ምኞት ነው የመለሰለት። ግርማዬ  በህይወት ለተወሰኑ ሳምንታትና ወራት ቢቆይ ኖሮ በአፉ ጎርሶ አጣጥሞ ለመዋጥ ተስኖት ቀሪው እድሜው በህክምና ሳይረዳ በልቶ ማደር እንደሚሳነው በልባችን የተረዳነው ነገር ግን በአንደበታችን ያልተናገርነው ሚስጥር ነበር።

አባቴ በህይወት ብትለየኝም ከዚህ ወደተሻለ ፣ሁልጊዜ በጸሎትህ ወደለመንከውና ወደምትናፍቀው ቦታ ስለሄድክ በውስጤ ደስታ ይሰማኛል። አንተ ለፍተህ እና ተግተህ ለዚህ ስላበቃህን እና አሁንም በመጨረሻ እንተ አልፈህ እኛ የህይወት ህልማችንንና ኑራችንን እንድናሳካ ምክንያት ስለሆንክ አመሰግንካሃለው። በቀሪ ሕይወቴ ስምህን በበጎ ላነሳ እናም መልካም አባትነትህን ለልጆቼና ለልጅ ልጆቼ ልመሰክር ቃል እገባልሃለው።  ታድያ አደራ እንተም የኔንም ሆነ የሌሎቹን የወደፍት ስኬቶች ያው እንደተለመደው ቀመም እያደረግክ በገነት ላሉት ማውራት አትዘንጋ። Do not worry, I will always try to make you proud.  አስኩይንም ለኔ ተውልኝ። እኔ ብቻ አንድ አስራ ምናምን Grandchildren አሸክሚ ነው የምልክልህ።

አወድካልው እዛው እንገናኝ
የመጀመሪያ ልጅህ
ያሬድ ግርማ

በዚው አጋጣሚ፣ I wanted to thank those who supported and counseled our father and family during our trying times. እኛ ልጆቹ ባለማወቅም ሆነ ባለመቻል ያልሆንንለት እና ልናደርግለት ያልቻልነውን ያደረጋቹለት፣ የጸለያችሁለት የደገፋችሁት የመከራችሁት እና ያጽናናችሁት ሁሉ (የአክስታችን ቤዛ ቤተሰብ እና የመድሃኒአለም ቤተክርስቲያን ምዕመናን፣ ሽማግሌዎች፣ ፓስተር ግርማ and Bible study ጓደኞቹ), ምስጋናችን ከልብ የመነጨ ነው። እግዚአብሄር ብድራቱን ይክፈላችሁ።

አሁንም እናታችን as she copes living without her husband of 40 years on her side, አደራ የምንሰጠው ለእ/ር እና ለእናንተው ነው።

አመሰግናለሁ

Would you Like to Leave a Note?

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *